ትውልድን የማብቃት አለም

ትውልድን የማብቃት አለም አቀፍ ሁለንተናዊ አገልግሎት እኛ ፍጥረቱ ነን እና ፤እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።

ኤፌ 2፡10

“ልታየው የምትፈልገውን ለውጥ ሆነህ ተገኝ“

“ልታየው የምትፈልገውን ለውጥ ሆነህ ተገኝ“

ማህተመ ጋንዲ

የተገለጠውን የእግዚአብሔርን

የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፍቅር እና እውነት ለትውልድ ሁሉ በትምህርት እና በተግባር ደርሶ ማየት፡፡

ራዕይ

እንኳን በደህና መጡ

የጌታችን የኢየሱስን ክርስቶስን እርምጃ በመከተል በኢትዮጲያ እንዲሁም በምድር ሁሉ ዙርያ ባሉ ማህበረሰብ መካከል ዘላቂ የሆነ ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመጣ የሚሰራ አገልግሎት ነው፡፡ የአገልግሎታችን ማዕከል እምነት ተኮር የሆነ ሁለንተናዊ እሴቶችን በመያዝ ለማህበረሰብ ችግሮች መፍትሔ እንፈልጋለን፡፡ ይህንንም እውን ለማድረግ በመሪነት፣በትምህርት፣በስልጠና እና በሁለንተናዊ ማህበረሰብ ተኮር የልማት ስራ እንሰራን፡፡

አመራርና ልዕቀት

በአመራር እና ልዕቀት ዙርያ የአሰልጣኞች ወርክሾፕ በመስጠት ለቤተ-ክርስቲያን፣ለማህበረሰቡ መሻሻል፣ ማደግ፤ መንፈሳዊነት፣ወጣት እና የማህበረሰብ መሪዎችን ላይ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት እንሰራለን፡፡

ትምህርትና ሥልጠና

እውነተኛ እና ዘላቂ የሆነ ለውጥ በማህበረሰብ ውስጥ መምጣት የሚችለው በዕቅድ እና የታሰበበት ትምህርት መስጠት ሲቻል ነው፡፡ በመሆኑም የማብቃት ዓለም ዓቀፍ ሁለንተኛዊ አገልግሎት በትምህርት እና ሥልጠና አዕምሮአዊ ብቻ ሳይሆን ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት እንሰራለን፡፡

ጥናት እና መጽሐፍት ዝግጅት

ጥናቶች እና መጽሐፍት ለተሻለ እና በዕውቀት የታገዘ መስተጋብርን በማህበረሰቡ ውስጥ ለመፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤  የማብቃት ዓለም ዓቀፍ ሁለንተኛዊ አገልግሎት አንዱ ስራው ጥናቶችን፣መጽሐፍትን እና ማንዋሎችን በመስራትና በማሰራጨት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡

ሁለንተናዊ የማዕበረሰብ ተኮር ልማት

ትውልድን የማብቃት ዓለም ዓቀፍ ሁለንተኛዊ አገልግሎት (Generation Empowerment International Holistic Ministry) ከቤተ-ክርስቲያን ጋር በመተባበር ማህበረሰብ ተኮር የሆኑ ለውጥን ለማምጣት የልማት ስራዎች ይሰራል፡፡ አገልግሎቱም ከድህነት ቅነሳ፣ ገቢ ማስገኛ፣ ብድርና ቁጠባ እንዲሁም ማህበረሰቡን ማስታጠቅ ላይ ተነሳሽነትን በመውሰድ ዘላቂ የሆነን ለውጥ ለማምጣት ይሰራል፡፡

ወንጌል ስርጭት፣ቤተ-ክርስቲያን ተከላ እና ደቀ-መዛሙርት ማፍራት

ለቤተ-ክርስቲያን መስፋት፣ ማደግ እና መለምለም ትውልድን የማብቃት ዓለም ዓቀፍ ሁለንተኛዊ አገልግሎት ዋናና ማዕከላዊ የሆነ አላማው ነው፡፡ በወንጌል ስርጭት ስራዎች፣ቤተ-ክርስቲያን ተከላ እንዲሁም በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ያለ የደቀ-መዝሙር የማፍራት ስራዎች ወደ ፍሬ እንዲመጡ አብሮ ይሰራል፡፡

አብራችሁን ፀልዮ

  • በኢትዮጵያ ያለችው ወንጌላዊት ቤተ-ክርስቲያን ምድሪቱ እየገጠማት ላለው መከራ መፍትሔ እንድትሆን፡፡
  • አገልግሎታችንን እየጀመርን በመሆኑ፤መለኮታዊ ምሪትን መከተል እንድንችል

ፈቃደኛ ሰራተኞች አጋሮች

ፈቃደኛ ሰራተኞች

ትውልድን ለማጎልበት በምናደርገው ጥረት ፤ ከእኛ ጋር በጎ ፈቃደኞች ይሁኑ

በጎ ፈቃደኞች ይሁኑ

በማዳረስ ተልእኮዎች ላይ መሳተፍ

የሥራ ስርዓቶችን ማደራጀት እና ማዋቀር

አጋራችን ይሁኑ

ትውልድን ለማጎልበት በምናደርገው ጥረት ፤ የእኛ አጋር ይሁኑ

በልማት ሥራ ላይ ለማህበረሰቡን ይድረሱ

ሚሽን እና የቤተክርስቲያን ተከላ ስራዎች

ለወንጌል ስራ ቁሳቁስ ማዘጋጀት

የወደፊት መሪዎችን ማሰልጠን እና ማዘጋጀት