1. ከፍጥረት በፊትና በኋላ በራሱ የሚኖር፣ የሚታዩትንና የማይታዩትን በሙሉ በፈጠረ፣ ለሕልውናው ምክንያት በሌለው በአንድ እግዚአብሔር እናምናለን፡፡
  2. በአንድነቱ ውስጥ በመለኮተ ባህርይ አንድ የሆኑ  ህላዌ ሶስትነት ውስጥ ለዘላለም እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ እንዲሁም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በመለኮትነት ይኖራሉ፡፡
  3. ሰው በእግዚአብሔር መልክ እና አምሳል መልካም ሆኖ ቢፈጠርም፤ በገዛ ፈቃዱ ኃጥያትን በመስራት ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ተለያየ፤ ይህን በክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋ በነጻ የሆነ ድነት ብኣ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ይችላል፡፡
  4. በኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም መወለድ፣ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ መሞትና መቃብርን ፈንቅሎ መነሳት፣ ወደ ሰማይ ማረግ፣ ዳግም እንደሚመጣ እናምናለን፡፡
  5. ማንኛውም ሰው የኃጢያት ስርየትና የዘለዓለም ሕይወት ሊያገኝ የሚችለው ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው በሆነው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ እንደሆነ እናምናለን፡፡
  6. በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ሙላት ፣ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን የገለጻቸው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በሙሉ ዛሬም ልንቀበላቸውና ልንለማመዳቸው እንደሚገባ፣ ምዕመናንም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው በሕይወታቸው ፍሬው ሊታይ እንደሚገባ እናምናለን፡፡
  7. መጽሐፍ ቅዱስ 39 የብሉይ ኪዳንና 27 የአዲስ ኪዳን መጽሐፍት እንዳሉት፣ 66ቱም በእግዚአብሔር እስትንፋስ እንደተጻፉ፣ የቤተክርስቲያን ብቸኛና እውነተኛ የሥልጣን ምንጭ እንደሆኑ እናምናለን፡፡
  8. በቅዱሳንና በክፉ መላዕክት መኖር፣ ገሃነም እሳት የተፈጠረው ለሰይጣንና ለመላዕክቱ እንደሆነ እናምናለን፡፡
  9. አማኞች ሁለንተናዊ ለሆነ የቅድስና እና የጽድቅ ህይወት ክርስቶስ ኢየሱስን ለመምሰል እንደተጠሩ እናምናለን፡፡
  10. በዳግም ምፅዓት፣ በሕያዋንና በሙታን ትንሣኤ፣ በዘለዓለም ሕይወትና ፍርድ፣ በመንግሥተ ሰማይና በገሃነም እሳት መኖር እናምናለን፡፡
  11. የሚሆነው፣ የሆነው እና ሊሆን ያለው በሙሉ ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ እንደሆነ እናምናለን፡፡