- ከፍጥረት በፊትና በኋላ በራሱ የሚኖር፣ የሚታዩትንና የማይታዩትን በሙሉ በፈጠረ፣ ለሕልውናው ምክንያት በሌለው በአንድ እግዚአብሔር እናምናለን፡፡
- በአንድነቱ ውስጥ በመለኮተ ባህርይ አንድ የሆኑ ህላዌ ሶስትነት ውስጥ ለዘላለም እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ እንዲሁም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በመለኮትነት ይኖራሉ፡፡
- ሰው በእግዚአብሔር መልክ እና አምሳል መልካም ሆኖ ቢፈጠርም፤ በገዛ ፈቃዱ ኃጥያትን በመስራት ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ተለያየ፤ ይህን በክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋ በነጻ የሆነ ድነት ብኣ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ይችላል፡፡
- በኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም መወለድ፣ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ መሞትና መቃብርን ፈንቅሎ መነሳት፣ ወደ ሰማይ ማረግ፣ ዳግም እንደሚመጣ እናምናለን፡፡
- ማንኛውም ሰው የኃጢያት ስርየትና የዘለዓለም ሕይወት ሊያገኝ የሚችለው ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው በሆነው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ እንደሆነ እናምናለን፡፡
- በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ሙላት ፣ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን የገለጻቸው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በሙሉ ዛሬም ልንቀበላቸውና ልንለማመዳቸው እንደሚገባ፣ ምዕመናንም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው በሕይወታቸው ፍሬው ሊታይ እንደሚገባ እናምናለን፡፡
- መጽሐፍ ቅዱስ 39 የብሉይ ኪዳንና 27 የአዲስ ኪዳን መጽሐፍት እንዳሉት፣ 66ቱም በእግዚአብሔር እስትንፋስ እንደተጻፉ፣ የቤተክርስቲያን ብቸኛና እውነተኛ የሥልጣን ምንጭ እንደሆኑ እናምናለን፡፡
- በቅዱሳንና በክፉ መላዕክት መኖር፣ ገሃነም እሳት የተፈጠረው ለሰይጣንና ለመላዕክቱ እንደሆነ እናምናለን፡፡
- አማኞች ሁለንተናዊ ለሆነ የቅድስና እና የጽድቅ ህይወት ክርስቶስ ኢየሱስን ለመምሰል እንደተጠሩ እናምናለን፡፡
- በዳግም ምፅዓት፣ በሕያዋንና በሙታን ትንሣኤ፣ በዘለዓለም ሕይወትና ፍርድ፣ በመንግሥተ ሰማይና በገሃነም እሳት መኖር እናምናለን፡፡
- የሚሆነው፣ የሆነው እና ሊሆን ያለው በሙሉ ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ እንደሆነ እናምናለን፡፡