አመራርና ልዕቀት

በአመራር እና ልዕቀት ዙር ያስልጠናዎች፣ ወርክሾፕ በመስጠት ለቤተ-ክርስቲያን፣ለማህበረሰቡ መሻሻል፣ ማደግ፤ መንፈሳዊነት፣ወጣት እና የማህበረሰብ መሪዎችን ላይ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት እንሰራለን፡፡

ትምህርትና ሥልጠና

እውነተኛ እና ዘላቂ የሆነ ለውጥ በማህበረሰብ ውስጥ መምጣት የሚችለው በዕቅድ እና የታሰበበት ትምህርት መስጠት ሲቻል ነው፡፡ በመሆኑም የማብቃት ዓለም ዓቀፍ ሁለንተኛዊ አገልግሎት በትምህርት እና ሥልጠና አዕምሮአዊ ብቻ ሳይሆን ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት እንሰራለን፡፡

ጥናት እና መጽሐፍት ዝግጅት

ጥናቶች እና መጽሐፍት ለተሻለ እና በዕውቀት የታገዘ መስተጋብርን በማህበረሰቡ ውስጥ ለመፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤  የማብቃት ዓለም ዓቀፍ ሁለንተኛዊ አገልግሎት አንዱ ስራው ጥናቶችን፣መጽሐፍትን እና ማንዋሎችን በመስራትና በማሰራጨት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡

ሁለንተናዊ የማዕበረሰብ ተኮር ልማት

ትውልድን የማብቃት ዓለም ዓቀፍ ሁለንተኛዊ አገልግሎት ከቤተ-ክርስቲያን ጋር በመተባበር ማህበረሰብ ተኮር የሆኑ ለውጥን ለማምጣት የልማት ስራዎች ይሰራል፡፡ አገልግሎቱም ከድህነት ቅነሳ፣ ገቢ ማስገኛ፣ ብድርና ቁጠባ እንዲሁም ማህበረሰቡን ማስታጠቅ ላይ ተነሳሽነትን በመውሰድ ዘላቂ የሆነን ለውጥ ለማምጣት ይሰራል፡፡

ወንጌል ስርጭት፣ቤተ-ክርስቲያን ተከላ እና ደቀ-መዛሙርት ማፍራት

ለቤተ-ክርስቲያን መስፋት፣ ማደግ እና መለምለም ትውልድን የማብቃት ዓለም ዓቀፍ ሁለንተኛዊ አገልግሎት ዋናና ማዕከላዊ የሆነ አላማው ነው፡፡ በወንጌል ስርጭት ስራዎች፣ቤተ-ክርስቲያን ተከላ እንዲሁም በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ያለ የደቀ-መዝሙር የማፍራት ስራዎች ወደ ፍሬ እንዲመጡ አብሮ ይሰራል፡፡