የጌታችን የኢየሱስን ክርስቶስን እርምጃ በመከተል በኢትዮጲያ እንዲሁም በምድር ሁሉ ዙርያ ባሉ ማህበረሰብ መካከል ዘላቂ የሆነ ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመጣ የሚሰራ አገልግሎት ነው፡፡ የአገልግሎታችን ማዕከል እምነት ተኮር የሆነ ሁለንተናዊ እሴቶችን በመያዝ ለማህበረሰብ ችግሮች መፍትሔ እንፈልጋለን፡፡ ይህንንም እውን ለማድረግ በመሪነት፣በትምህርት፣በስልጠና እና በሁለንተናዊ ማህበረሰብ ተኮር የልማት ስራ እንሰራን፡፡

መፍትሔ በጽድቅ እና ቅድስና የሚኖር ትውልድ በምታፈራ ቤተ-ክርስቲያን እንደሚጀምር እና መጀመርም እንዳለበት እናምናለን፤በመሆኑም ትውልድን የማብቃት ዓለም ዓቀፍ ሁለንተናዊ አገልግሎት በቀጥታ ከቤተ-ክርስቲያን፣ከመንፈሳዊ ተቋማት ጋር እንዲሁም መሪዎች እና አገልጋዮችን በማስታጠቅ የሚሰራ ነው፡፡ዘለቄታዊ እና ስር-ነቀል የሆነን ለውጥ በጠቅላላው ማህበረሰብ ውስጥ እንዲሰፍን ቤተ-ክርስቲያን ትልቁን ሚና መጫወት የምትችል እንደመሆኗ አብሮ ለውጥን ለማምጣት እንሰራለን፡፡

አጭር ታሪክ

ሁለንተናዊ ማስታጠቅ

መሰረታዊ ፍላጎቶች ሰርፆ በሚናወጥ ማህበረሰብ ውስጥ ስር-ሰደድ የሆነ በመሪዎች እና በሚረዱ የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል የነበረው ብቃት ማነስ የጎላ እና እጅግ ሰፊ ነበር፡፡ ትውልድን የማብቃት ዓለም ዓቀፍ ሁለንተናዊ አገልግሎት መስራች እና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጌድዮን ተሊላ መፍትሔውን ሲያስቡ የችግር እና የፍላጎትን መርታት ብቻ ሳይሆን በታጠቀ የማህበረሰብ ማንነት ውስጥ በመሆን ከነባራዊ አሰራር በመላቀቅ ዘለቄታዊነት ያለውን ለውጥ በማምጣት መሰራት እንዳለበት ያምናሉ፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አቶ ጌድዮን ተሊላን በልጅነታቸው አግኝቶአቸው በአካሉ በሆነች ቤተ-ክረስቲያን ውስጥ የማደግን እና የማገልገልን ዕድል ሲሰጣቸው፤የእግዚአብሔን ኃያል ስራ እና የማይመክን ተስፋ በእጃቸው ከሚነካው አካሉ በላይ እውን እንደሆነ አስተማራቸው፡፡ በዚህም ግንኙነት ውስጥ  ይህ ራዕይ ተወለደ፡፡ ከቤተ-ክርስቲያን ጀምሮ እስከ ማህበረሰቡ ድረስ የሚፈስ ትውልድን የሚያስታጥቅ ትልቅ ራዕይ፡፡

ሰላም፤ምድር ከሰማይ የምትቀምስበት ማንነት የሚሰፍነው ቤተ-ክርስቲያን የተሰጣትን የክርስቶስን ወንጌል እንደሚገባ በመስበክ እና በመኖር ውስጥ መሆኑን አቶ ጌድዮን ተሊላ. አጥብቀው ያስተምራሉ፡፡ ይህም በውስጣቸው የሚቀጣጠልን ትንሽ ራዕይን፣አካል ለብሶ እግዚአብሔር ይሰራው ዘንድ የጠራውን እውነት ለመኖር ከቤተ-ክርስቲያን በመጀመር እስከ አለም ዳርቻ ድረስ ያለውን እንዲሁም የሚመጣውን ትውልድ ‹ሁለንተናዊ ማስታጠቅን› ለመስራት ቆርጠው ተነስተዋል፡፡

ራዕይ

የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፍቅር እና እውነት ለትውልድ ሁሉ በትምህርት እና በተግባር ደርሶ ማየት፡፡

ተልዕኮ

  • በመንፈሳዊ እና ልማታዊ ተቋማት ውስጥ የተሻለ አመራርን ማስፈን
  • በክርስቶስ ኢየሱስ የማያምኑ ሰዎችን በወንጌል መድረስ
  • በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ደቀ-መዛሙርትን በማስተማር ማሳደግ
  • የቤተ-ክርስቲያን አገልጋዮችን፣የተለያዩ ቢሮ ሰራተኞችን፣ተተኪ መሪዎችን ለእግዚአብሔር መንግስት ሥራ ማዘጋጀት ማፍራት እና ማብቃት፣
  • የልማት ስራዎችን ለማሳለጥ ከመንፈሳዊ ተቋማት ጋር መስራት

ግብ

  • የመንፈሳዊ ተቋማትን አመራር እና የሰው ኃይል ማብቃት
  • ለሰዎች ወንጌል በመስበክ እና የክርስቶስ ደቀ-መዛሙርት እንዲሆኑ ማስተማር
  • አገልጋዮች በተሟላ ስብዕናና መንፈሳዊ ብቃት ቤተ-ክርስቲያንን እንዲመሩና እንዲያገለግሉ ማገዝ
  • መንፈሳዊ ተቋማትን እና ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ የጥናትና የመጽሐፍት ህትመት ስራዎችን ማበርከት
  • ከመንፈሳዊ ተቋማት ጋር በመተባበር ሁለንተናዊ ማህበረሰብ ተኮር የሆኑ ስራዎችን መስራት

እሴቶች

  • እውነትናፅድቅ
  • ታማኝነት
  • ሐቀኝነት
  • የሰውን ዘር ሁሉ ያለ አድሎ ማገልገል
  • ግልጽነት
  • ተጠያቂነት

ህጋዊነት

የተቋቋመበት ግዜ፡ ጥር 2014